አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች፣ የእምነቱ ተከታይ ለሆኑ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ እንዲሁም የቀድሞ ምሩቃን እንኳን ለስቅለትና ትንሣኤ በዓላት በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የጤናና የፍቅር እንዲሆን ከወዲሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡

የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን በ2016 ዓ.ም የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶችን ለሁሉም ህጋዊ አቅራቢዎች/ነጋዴዎች/ተደራሽ ለማድረግ፣ የተቋማት ብልሹ አሠራሮችን ለመከላከል እንዲሁም ሁሉንም አቅራቢዎች/ነጋዴዎች እኩል ለማሳተፍ የግዥ ሥርዓቱን በማዘመን ግልፅና ቀልጣፋ አሠራር በመዘርጋት ማንኛውም ግዥ በኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሥርዓት “eGP/electronic Government Procurement” ብቻ ግዥ እንዲፈፀም መወሰኑ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሠረት አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ማንኛውንም ግዥ በኤሌክትሮኒክስ የመንግሥት ግዥ ሥርዓት /eGP/ ለመፈፀም ሙሉ በሙሉ ሥርዓቱን በመዘርጋት ተግባራዊ በማድረግ ላይ የሚገኝ በመሆኑ በአርባ ምንጭ ከተማና ዙሪያው የሚትገኙ አቅራቢ ህጋዊ ነጋዴዎች በመንግሥት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን ኤጀንሲ ምዝገባ በማድረግ በኤጀንሲ ድኅረ ገጽ ላይ በሚለቀቁ ግዥዎች ላይ እንድትሳተፉ ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል፡፡

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ፈጠራ ልማት ማበልጸጊያ ማዕከል የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር ላሸነፉ ተማሪዎች ሽልማት እና በዕውቅ የሥራ ፈጠራ አማካሪና ደራሲ ቁልፍ መልእክት የማስተላለፍ መርሃ ግብር ሚያዝያ 17/2016 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሀገር በቀል ዕውቀት ለሥራ ፈጠራ፣ ለቁጠባና ለዘላቂ ሰላም በሚል ርእስ ሀገር አቀፍ የምርምር ዐውደ ጥናት ሚያዝያ 19/2016 ዓ/ም አካሂዷል፡፡ተጨማሪ ፎቶዎችን ለማየት እዚህ ይጫኑ፡፡

Arba Minch University hosted the 10th national symposium on Research for Development on 26th April, 2024 in Main Campus. Researchers from across universities of Ethiopia and PhD candidates from South Africa and Germany participated in the event. Click here to see more photos.